✝✝✝ እንኩዋን ለቅድስት ኤልሳቤጥ: ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ሊቅ እና አባ ሳዊርያኖስ ክቡር ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✝✝
✝✝✝ ቅድስት ኤልሳቤጥ ✝✝✝
=>በወንጌላዊው አንደበት የተመሰገነች እናታችን ቅድስት ኤልሳቤጥ ትውልዷ ከነገደ ሌዊ ነው:: ሐረገ ሙላዷም ከቅዱስ አሮን ካህን ወገን ይመዘዛል:: ከአሮን በቴክታና በጥሪቃ ወርዶ ሔርሜላ ላይ ይደርሳል::
+ይህቺ ሔርሜላ የምትባል ደግ ሴት ማጣት ("ጣ" ጠብቆ ይነበብ) የሚባል የተባረከ ሰው አግብታ 3 ቡሩካት ልጆችን ወለደች:: የመጀመሪያዋን 'ማርያም' አሏት:: እርሷ ቅድስት ሰሎሜን ወለደች:: ሁለተኛዋን 'ሶፍያ' አሏት:: እርሷ ደግሞ ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደች::
+ሦስተኛዋ ግን የተለየች ናት:: 'ሐና' ብለው ሰየሟት:: እርሷም የሰማይና የምድር ንግሥት የሆነችውን ድንግል ማርያምን ወለደች:: በዚህም መሠረት ድንግል ማርያም: ቅድስት ኤልሳቤጥና ቅድስት ሰሎሜ የእህትማማች ልጆች ናቸው::
+ቅድስት ኤልሳቤጥ እድሜዋ በደረሰ ጊዜ ስም አጠራሩ የከበረ: ደግ ካህን ለሆነ: ለቅዱስ ዘካርያስ አጋቧት:: እርሷ የሊቀ ካህናቱ ሚስት ናትና ክብሯ ከፍ ያለ ነበር:: ምንም ልጅ ባይኖራትም ዘወትር በጸሎትና በጾም: ምጽዋትንም በማዘውተር: ነዳያንንም በማሰብ የምትኖር እናትም ነበረች::
+ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል::
"ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)
+የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል! እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር::
+ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው:: ቅድስቲቷ መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች::
+ድንግል እመቤታችን ወደ እርሷ መጥታ 'ሰላም' ባለቻት ጊዜ ምንም ያሳደገቻት ልጇ ማለት ብትሆን: መንፈስ ቅዱስ ስለ ሞላባት እመ ብርሃንን አመስግናታለች:: ቡርክት: ብጽእት: ከፍጥረተ ዓለሙ የከበረች መሆኗንም መስክራለች::
+በማሕጸኗ ያለ የ6 ወር ጽንስም የእመ አምላክን ድምጽ ቢሰማ በደስታ ዘሏል:: ለፈጣሪውም ስግደተ-ስባሔ አቅርቧል:: ቅድስት ኤልሳቤጥ አክላም "ወምንትኑ አነ ከመ ትምጽኢ ኀቤየ እሙ ለእግዚእየ-የጌታየ እናቱ ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይገባኛል?" ስትል በትኅትና ተናግራለች:: ከጌታ እናት ጋር ለ3 ወራት በአንድ ቤት ቆይታለች::
+ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ 2 ዓመት ከ6 ወር በሆነው ጊዜ ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" አሉ::
+እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ3 (5) ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ 5 (7) ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና ስምዖን ወርደው ቀበሯት:: ኤልሳቤጥ ማለት 'እግዚአብሔር መሐላየ ነው': አንድም 'የጌታ አገልጋይ' ማለት ነው::
+" ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ሊቅ "+
=>ይህ አባት የተዋሕዶ ሃይማኖታችን ምሰሶ ነው:: በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በግብጽ ተወልዶ አድጐ: በልጅነቱ መጻሕፍትን ተምሮ: የምናኔ ሕይወትን መርጧል:: ቆይቶም የታላቁ ሊቅ ቅዱስ ቄርሎስ ረድእ ሆኖ ተምሯል: አገልግሎታል::
+በጉባኤ ኤፌሶን ጊዜም ቅዱስ ቄርሎስን ተከትሎ ሒዶ ተሳትፏል:: በ444 ዓ/ም ታላቁን ሊቅ ተክቶ የእስክንድርያ 25ኛ ፓትርያርክ ሆኖ ተሹሟል:: ለ7 ዓመታትም መጽሐፈ ቅዳሴውን (እምቅድመ ዓለምን) ጨምሮ ብዙ ድርሰቶችን ደርሷል:: በመልካም እረኝነትም ሕዝቡን ጠብቇል::
+ዘመነ ሰማዕታትን ተከትሎ የመጣው የመናፍቃን ዘመን ሲሆን ለ150 ዓመታት ያህል መናፍቃን እንደ አሸን ፈልተዋል:: በዚያው ልክ ከዋክብት ቅዱሳን ሊቃውንት ነበሩና በየጊዜው ጉባኤያትን እየሠሩ: መናፍቃንን አሳፍረዋል:: ምዕመናንንም አጽንተዋል::
+በ451 ዓ/ም የተፈጸመው ድርጊት ግን ዛሬም ድረስ ጠባሳው የሚለቅ አልሃነም:: ንጉሡ መርቅያንና ዻዻሱ ልዮን የንስጥሮስን ትምሕርት አለባብሰው ሊያስተምሩ ሲሞክሩ ግጭት በመፈጠሩ ቤተ ክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ 2 ተከፈለች::
+በጉባኤው የነበሩ 636 ዻዻሳት ስቃይና ሞትን ፈርተው በኑፋቄ መጽሐፍ ላይ በመፈረማቸው "መለካውያን" (ከእግዚአብሔር ይልቅ ለንጉሥ የሚታዘዙ) ተባሉ:: ጉባኤውም "ጉባኤ ከለባት" (የውሾች ስብሰባ): "ጉባኤ አብዳን" (የሰነፎች ጉባኤ) ተብሏል::
+ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ግን "በኑፋቄው ላይ አልፈርምም" ከማለቱ አልፎ መናፍቃኑን አወገዛቸው:: በዚህ ምክንያት ወደ ጋግራ ደሴት ከ7 ደቀ መዛሙርቱ ጋር አሳደዱት:: በዚያም ለ3 ዓመታት ቆይቶ በ454 ዓ/ም ዐረፈ::
+ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ከማረፉ በፊት በተሰደደባት ደሴተ ጋግራ ለ3 ዓመታት ብዙ መከራ ከመናፍቃን ደርሶበታል:: እርሱ ግን በትእግስቱና በትምሕርቱ ብዙዎችን ወደ ሃይማኖት መልሷል::
+ቤተ ክርስቲያን እርሱን 'አበ ተዋሕዶ' (የተዋሕዶ እምነት አባትና አርበኛ) ትለዋለች:: የተነጨ ጺሙ: የረገፉ ጥርሶቹና የፈሰሰ ደሙ ዛሬም ድረስ ትልቅ ምስክርና የሃይማኖት ፍሬ ነውና::
"ያስተጻንዕ ህየ እለ ኀለዉ ደቂቀ:
ዘተነጽየ እምነ ጽሕሙ ወእም አስናኒሁ ዘወድቀ:
ፍሬ ሃይማኖቱ ፈነወ ብሔረ ርሑቀ" እንዲል::
+" ታላቁ አባ ሳዊርያኖስ "+
=>የዚህን ቅዱስ ሰው ስም የሚጠራ አፍ ክቡር ነው:: ጣዕመ ሕይወቱ ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም:: እርሱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የበቀለ: 30: 60: 100 ፍሬዎችን ያፈራ የመንፈስ ቅዱስ ተክል ነው:: በትውልድ ሮማዊ ሲሆን የተወለደው በ309 ዓ/ም ነው::
+ወላጆቹ በዚህ የንጉሥ ዘመዶች: በዚያ ደግሞ ባለጠጐች ነበሩ:: እነርሱ ለልጃቸው ጥበብን መርጠዋልና የግሪክን ፍልስፍና: የዮናናውያንን ጥበብ ሁሉ ተማረ:: ከዚያ በአንድ ልቡ ብሉይን: ሐዲስን ተምሮ ሲጠነቅቅ ወላጆቹ ዐረፉ::
+ቅዱሱ ሳዊርያኖስም "የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር መስጠት አለብኝ" ብሎ ቀን ቀን ያለፈውን: ያገደመውን ሁሉ ሲያበላ: ሲያጠጣ: ነዳያንን ሲጐበኝ ይውላል:: ምሽት ሲል ደግሞ ወደ ቅዱሱ ንጉሥ (አኖሬዎስ) ቤተ መንግስት ገብቶ: ወገቡን ታጥቆ ከንጉሡ ጋር ሲጸልይና ሲሰግድ ያድራል::
+ውዳሴ ከንቱ ሲበዛበት ንብረቱን ሁሉ ለነዳያን አካፍሎ ገብላ ወደምትባል ሃገር ሒዶ መነኮሰ:: ባጭር ጊዜም የብዙ ነፍሳት አባት ሆነ:: ብዙ ተአምራትንም ሠራ:: ትንሽ ቆይቶ ደግሞ የገብላ (ኤላ) ዻዻስ ሆኖ ተሾመ:: በዘመነ ሲመቱም እንቅልፍን አልተመለከተም:: ባጭር ታጥቆ ያላመኑትን ለማሳመን ደከመ እንጂ::
+ጌታ ከእርሱ ጋር ነውና አይሁድን: መተተኞችንና አሕዛብን ሁሉ አሳምኖ ኤላ (ገብላ) አንድ የክርስቶስ መንጋ ሆነች:: የሚገርመው ከደግነቱ የተነሳ ሰይጣንን እንዳይገባ ከልክሎት በመንገድ ላይ ቁሞ ሲያለቅስ ይታይ ነበር:: ቅዱስ ሳዊርያኖስ ብዙ ድርሳናትን ደርሶ: እልፍ ፍሬንም አፍርቶ: በተወለደ በ100 ዓመቱ በ408 ዓ/ም ዐርፎ በክብር ተቀብሯል::
=>የእነዚህ ሁሉ ከዋክብት ቅዱሳን አምላክ ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን:: ክፉውንም ሁሉ ያርቅልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
=>መስከረም 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.እናታችን ቅድስት ኤልሳቤጥ
2.ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ሊቅ (የተዋሕዶ ሃይማኖት አባት)
3.ታላቁ ቅዱስ ሳዊርያኖስ
4.ቅድስት ሐና (የእመ ብርሃን እናት-ልደቷ ነው)
5.ቅዱሳን አጋቶን: ዼጥሮስ: ዮሐንስ: አሞንና እናታቸው ራፊቃ (ሰማዕታት)
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላ ገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)
=>+"+ ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ጽንሱ በማሕጸኗ ውስጥ ዘለለ:: በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት:: በታላቅ ድምጽም ጮኻ እንዲህ አለች:- 'አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ: የማሕጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው:: የጌታየ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? . . . ከጌታ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብጽዕት ናት:: +"+ (ሉቃ. 1:41)
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ ፫:፫/
ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together
https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━━

Comments
Post a Comment