✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖
❖ ግንቦት 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+"+ አርዋ ቅድስት +"+
=>እናታችን ቅድስት አርዋ በስነ ገድላቸው ከደመቁ
የቀደመው ዘመን ቅዱሳት አንስት አንዷ ናት:: በሕጻንነቷ
የሚገባውን
የክርስትና ትምሕርት ተምራለችና ምርጫዋ ሰማያዊው
ሙሽርነት ሆነ::
+ለሰዎች ሕይወት እንቅፋት እየሆኑ ከሚያስቸግሩ ነገሮች
አንዱ መልክ ነው:: እግዚአብሔር የፈጠረውን ደም ግባት
(ቁንጅና)
በማይገባ ተጠቅመው የአጋንንት ራት የሆኑ: ሌሎችንም
አብረው ያጠፉ ሰዎች ቁጥራቸው እጅግ ብዙ ነው:: አርዋ
ግን ይሕ
ቀረሽ የማይሏት ውብ ብትሆንም እርሷ ለዚሕ ቦታ
አልነበራትም:: በለጋ እድሜዋ በክርስቶስና በድንግል እናቱ
ፍቅር ተጠመደች
እንጂ::
+ቅድስት አርዋ ሁሉ ያላት ስትሆን ስለ መንግስተ ሰማያት
ሁሉን ንቃለች:: በተለይ ደግሞ ሥጋዊ ፍትወትን ትገድል
ዘንድ
ያሳየችው ተጋድሎ በዜና ቤተ ክርስቲያን የተደነቀ በመሆኑ
"መዋኢተ ፍትወት" (የሥጋን ፍላጎት ድል የነሳች)
አስብሏታል::
+የሚገርመው የቅድስቷ እናታችን ሕይወት በጾምና
በጸሎት ብቻ የተወሰነ አልነበረም:: በሰው ሁሉ ፊት ብርሃን
መሆን የቻለ
የደግነት: ርሕራሔ: የፍቅርና የምጽዋት ሕይወትም ነበራት
እንጂ::
+አንድ ቀን በተንኮለኞች የሐሰት ምስክር ያለ ጥፋቷ
ለፍርድ ቀረበች:: ፍርደ ገምድል ዳኛ ሞት ፈረደባት::
በአደባባይ
በጭካኔ ቅድስት እናታችንን ገደሏት:: እግዚአብሔር ግን
ድንቅ ነውና ከሞት አስነስቷት ገዳዮቿ እንዲጸጸቱ
አድርጓል::
ከዚሕ በኋላም በንጹሕ አኗኗሯ ቀጠለች::
+አንድ ቀን ግን ከባድ ፈተና መጣባት:: አንድ በደም
ግባቷ ተማርኮ ሲፈልጋት የኖረ ጐልማሳ አሳቻ ሰዓትና ቦታ
ላይ
አገኛት:: የሥጋ ፈቃዱን ይፈጽም ዘንድ አስገደዳት::
+እርሱን መታገሉ ከአቅሟ በላይ ስለሆነባት እርሱ ልብሱን
እያወለቀ እርሷ ከወደቀችበት ሆና ወደ ፈጣሪዋ ለመነች:-
"ጌታየ
ሆይ! የእኔንም ድንግልና ጠብቅ: እርሱንም ኃጢአት
ይሠራ ዘንድ አትተወው:: ስለዚሕም ነፍሴን ተቀበላት" ብላ
አለቀሰች::
+እመቤታችን እንደ ዐይን ጥቅሻ ወርዳ ነፍሷን አሳረገች::
ጐልማሳው ወደ ጣላት ቅድስት ዘወር ቢል ሙታ አገኛት::
እርሱም
ተጸጸተ:: ወገኖቿ በዝማሬ እናታችን ቅድስት አርዋን
ቀብረዋታል::
✞ ቅዱስ ቆሮስ ሐዋርያ ✞
=>ዳግመኛ በዚህች ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ቆሮስ አርፏል::
+ቅዱስ ቆሮስ ከ72ቱ አርድእት አንዱ ሲሆን ከጌታችን
እግር የተማረ: ለስብከተ ወንጌል ብዙ ሃገራትን የዞረ ታላቅ
ሐዋርያ
ነው:: ባስተማረባቸው ቦታዎች ብዙ ሕማማትን
ተቀብሏል::
+ብዙ አሕዛብንም ወደ አሚነ ክርስቶስ መልሷል:: በተለይ
ከቅዱስ ዻውሎስ ጋር ለዓመታት አገልግሏል:: ቅዱስ
ዻውሎስ
ሲታሠር መልዕክቶችንም ይወስድለት ነበር::
❖ወርኀ ግንቦትን በሰላም ላስፈጸመን እግዚአብሔር
ክብርና ምስጋና ይሁን:: አምላካችን ከወዳጆቹ በረከትን
ይክፈለን::
❖ግንቦት 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት አርዋ እናታችን
2.ቅዱስ ቆሮስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ ዲማዲስ ሰማዕት
4.አባ ሚካኤል ሊቀ ዻዻሳት
❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ
2፡ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
3፡ አባ ሣሉሲ ክቡር
4፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ነባቤ መለኮት
5፡ ቅድስት ሶፍያና ሰማዕታት ልጆቿ
++"+ መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ:: አንቺ ግን
ከሁሉ ትበልጫለሽ::
ውበት ሐሰት ነው:: ደም ግባትም ከንቱ ነው::
እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች::
ከእጇ ፍሬ ስጧት:: ሥረዎቿም በሸንጐ ያመስግኗት:: +"+
(ምሳሌ. 31:29)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together
https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━
Comments
Post a Comment