◇ የቅዱሳት ሥዕላት አቀማመጥ በቤተ መቅደስ ◇
በቴዎድሮስ ስዩም።
⚜️⚜️⚜️✿✿✿✿✿✿✿✿✿⚜️⚜️⚜️
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቀኖና መሠረት ቅዱሳት ሥዕላት ራሱን የቻለ አቀማመጥ አላቸው፡፡ በቤተክርስቲያናችንም ቅዱሳት ሥዕላት ከቤተመቅደስ ጀምሮ በተለያዩ ቦታዎችና መንገድ ይቀመጣሉ፡፡ ይህንን ለመረዳት በተገቢው ቦታ ማስቀመጥ ያስፈልጋል፡፡ በቤተክርስቲያን ቤተመቅደስ ምዕመናን ሊያዩዋቸው በሚሉበት ሁኔታ ቅዱሳት ሥዕላት ይቀመጣሉ፡፡ የቅዱሳት ሥዕላቱ ዓይነትና የአቀማመጥ ሥርዓት እንደየቤተ ክርስቲያኑ ዕድሜ፣ ስፋትና ጥበት እና አሠራር ሊለያይ ይችላል፡፡ ሆኖም ግን በአብዛኛው አብያተ ክርስቲያናት በስፋት የምንመለከተው በጣሪያ ላይ ባሉ አግዳሚዎችና ቤተመቅደስ በሚገኙ በሮች እና መስኮቶች ላይ የመላእክት ሥዕሎች ይገኛሉ ይኸውም የቤተክርስቲያን ጠባቂነታቸውን ያጠይቃል፡፡ በሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በቅድስቱና በመቅደሱ እንዲሁም በቅኔ ማህሌቱና በቅድስቱ መካከል ባሉት ግድግዳዎች ላይ ደግሞ የተለያዩ ሥዕላት በየማዕዘናቱ (በየአቅጣጫው) ተሥለው ይገኛሉ ለምሳሌ፡-
◆መንበር ላይ
በሐዲስ ኪዳን ቤተመቅደስ ላይ በሚገኘው ታቦት መንበር ላይ የሚታየው የእመቤታችን ድንግል ማርያም ‹‹ምስለ ፍቁር ወልዳ፤ እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር›› ተብሎ የሚጠራው ሥዕል ይቀመጣል፡፡ ምክንያቱም ድንግል ማርያም ‹‹የሐዲስ ኪዳን ኪሩብ›› በመሆኗ ነው፡፡ አንድም ከኪሩቤል ስለምትበልጥ ምክንያቱም ዙፋኑን መሸከም ሳይሆን ለእሱ ዙፋን በመሆኗ፡፡ ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል ወትፈድፍድ እመሱራፌል እስመ ኮነት ታቦት ለአሐዱ ዘእምቅድስት ሥላሴ፤ ይህች ከኪሩቤል ትበልጣለች፤ ከሱራፌልም ትበልጣለች ከሦስት አካል ለአንዱ ማደሪያ ሆናለችና፡፡
◆በምስራቅ
ነገረ ኢየሱስ ይሣልበታል ይኸውም ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የፈጸማው ገቢር ተአምራት ወመንክራት፡፡ ገቢረ ሐዋርያት (የሐዋርያት ሥራና ተአምራት) እና እመቤታችን ቅዱስ ኤፍሬምን ስትባርከው የሚያሣዩ ሥዕላት ይሳሉባቸዋል፡፡ ከምህዋሩ በላይ ዕርገቱ ለእግዚነ ይሳላል፡፡
◆በምዕራብ
የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነገረ ልደቱ፣ ጥምቀቱ፣ ሕማማቱ፣ ስቅለቱ፣ ትንሣኤው፡፡ ምስለ ፍቁር ወልዳ በቀኝ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ በግራ ይሣላል፡፡ ከምህዋሩ በላይ የቅድስት ሥላሴ ሥዕል ይኖራል፡፡ በበሩ ላይ ደግሞ ቅዱስ ሚካኤል ፈርኦንን ከነሠራዊቱ እንዳሰመጠውና ቅዱስ ሩፋኤል ዓሣ አንበሪውን እንደወጋ ይሣልበታል፡፡ የቅዱሳን ተጋድሎም በዚሁ አቅጣጫ ይሣላሉ፡፡
◆በሰሜን
ሰማዕታት የሚሣሉበት አቅጣጫ ነው፡፡ የተለያዩ ሰማዕታትና ዕሞሙ ለሰማዕታት (የሰማዕታት እናታቸው) ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ጋር (ምስለ ፍቁር ወልዳ) እንዱሁም ከምህዋሩ በላይ ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን ሲገልጽ የሚያሳይ ሥዕል ይቀመጣል፡፡
◆በደቡብ
ነገረ ማርያም የሚደሳልበት ሲሆን ከልደቱ እስከ እርገቱ ያለውን ታሪክ የሚያሳይ ነው፡፡ በተጨማሪመ ነገረ ምጽአትን የሚገልጡ ሥዕላት ይቀመጣሉ፡፡ከምህዋሩ በላይ ደግሞ እመቤታችን በደብረ ምጥማቅ ያሳየችውን (ያደረገችውን) ተአምር የሚገልጥ ሥዕል ይቀመጣል፡፡ ይቆየን፡፡
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ ፫:፫/
ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ)እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈሚስጥር
🔊ሁሉም እንዲያነበው invite shareያርጉ
መንፈሳዊ ፅሁፎች፣ስእሎች ካሎት
@FasilKFCይላኩልን
✝ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር
Join Us Today And Lets learn Together
https://gondarmaheber.blogspot.com
https://t.me/Be_ente_semoa_le_mareyam
━━━━━━━༺✞༻━━━━━
Comments
Post a Comment