+ ሌላ መንገድ +
ለሰብአ ሰገል ለጌታ ከሰገዱ በኁዋላ ወደ ሔሮድስ ተመልሰው እንዳይሔዱ በሕልም ተነገራቸው:: ስለዚህ በሌላ መንገድ ወደ ሀገራቸው ሔዱ::
እግዚአብሔር ሰብአ ሰገል ብቻ ሳይሆኑ ሁላችንም ይህንን እንድናደርግ ይፈልጋል:: ለክርስቶስ ከሰገድን ወዲያ ወደ ሔሮድስ መመለስ ምንኛ ስኅተት ነው? በመንፈስ ጀምሮ በሥጋ መጨረስ : በስግደት ጀምሮ በኃጢአት መፈጸም በልደቱ ያገኘነውን ጸጋ ያሣጣናል::
ስዚህ የጌታን ልደት ካከበርህ በኁዋላ ድሮ በመጣህበት መንገድ አትመለስ:: ትናንት የተከተልከውን አቅጣጫ : ትናንት ደጅ የጠናኸውን ሔሮድስ ደግመህ አትመልከት::
እግዚአብሔር ለእርሱ ከሰገድህ በኁዋላ እግርህ ወደ ቀድሞው ሰፈር እንዲረግጥ አይፈልግም::
"ኢየሱስ ግን፦ ማንም ዕርፍ በእጁ ይዞ ወደ ኋላ የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም፡ አለ" ሉቃ. 9:62
Comments
Post a Comment